ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁለት ሙስሊሞች እርስ በርሳቸው እያንዳንዳቸው የባልደረባውን ህይወት ማጥፋትን ቋምጠው በሰይፋቸው ሊጋደሉ የተገናኙ እንደሆነ ሁለቱም እሳት እንደሚገቡ ተናገሩ። ገዳዩ ባለደረባውን በመግደሉ ምክንያት እሳት ውስጥ ይገባል። ሰሐቦች የተገዳዩ እሳት መግባት ግራ አጋባቸው: እንዴት የእሳት ይሆናል? ብለው ጠየቁ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረባውን ለመግደል በመጓጓቱ ፤ በገዳዩ ከመቀደም በስተቀር ከመግደል ምንም የከለከለው ነገር ስለሌለ እሱም ጭምር የእሳት መሆኑን ተናገሩ።