ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የትንሳኤ ቀን ተውበት እስካላደረጉ ወይም አላህ ቅጣቱን ይቅር እስካላላቸው ድረስ ቅጣት ስለሚገባቸው ሶስት የሰዎች አይነት ተናገሩ። የመጀመሪያው ቅጣት: የትንሳኤ ቀን አላህ በጣም ስለሚቆጣባቸው አያናግራቸውም። ይልቁንም እነርሱን ችላ ይላል። ወይም በነርሱ ላይ መቆጣቱን የሚጠቁም የማያስደስታቸውን ንግግር ያናግራቸዋል። ሁለተኛው ቅጣት: አያጠራቸውም፣ በነርሱ ላይ አያወድስም፣ ከወንጀላቸውም አያጠራቸውም። ሶስተኛው ቅጣት: በመጪው አለም አሳማሚና ብርቱ ቅጣት አላቸው። እነዚህም ሰዎች: የመጀመሪያው: ዝሙት ላይ የሚወድቅ ያረጀ ሰውዬ ነው። ሁለተኛው: ገንዘብ የሌለው ድሃ ከመሆኑም ጋር ሰዎች ላይ ይኮራል። ሶስተኛው: ሲሸጥና ሲገዛ በአላህ መማል የሚያበዛ ሰው ነው። በዚህም የአላህን ስም ዝቅ ያደርጋል። የአላህን ስምም ገንዘብ ማግኛ ያደርገዋል።