ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - በኢስራእና ሚዕራጅ ምሽት ወደ ሰማይ በወጡበት ወቅት የነሃስ ጥፍሮች ባሏቸውና ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውንም በሚቧጭሩና በሚቦጭቁ ሰዎች በኩል እንዳለፉ ተናገሩ። ነቢዩም - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም እነዚህ ሰዎች በዚህ ቅጣት እንዲመነዱ ያደረጋቸው ምንድነው? ብለው ጠየቁት። ጂብሪልም ዐለይሂ ሰላም እነዚህ ሰዎችን የሚያሙና ያለአግባብ ስለሰዎች ክብር የሚናገሩ ናቸው። ብሎ መለሰላቸው።