ነቢዩ(የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በዱንያ ውስጥ ሆን ብሎ ራስን ከማጥፋት አስጠነቀቁ። ይህን የፈፀመ ሰው የትንሳኤ ቀን በጀሃነም እሳት ውስጥ ነፍሱን በዱንያ በገደለበት መልኩ ራሱን ይቀጣል። ይህም ተስማሚ ቅጣት ነው። ነፍሱን ከተራራ ላይ ጥሎ የገደላት በጀሃነም እሳት ውስጥ ከሚገኝ ተራራ ወደ ጀሃነም ሸለቆዎች ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ነፍሱን በመጣል ራሱን ይቀጣል። መርዝ ጠጥቶ ነፍሱን የገደለ ሰውም በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ መርዙን በእጁ ይዞ ይጠጣዋል። ነፍሱን በስለት የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ስለቱን በእጁ ይዞ በርሱ ሆዱን እየወጋ ይኖራል።