ታቢዒዩ ማሊክ ቢን አውስ እርሱ ዘንድ በብር ዲርሃም ሊመነዝራቸው የፈለጋቸው የወርቅ ዲናሮች እንደነበሩት ተናገረ። ጦልሓ ቢን ዑበይዲላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ለርሱ "ዲናርህን አምጣና እንየው።" አለ። ቀጥሎ አይቶ ለመግዛት ከወሰነ በኋላ "የብሩን ዲርሃም እንድንሰጥህ በኋላ አገልጋያችን ከመጣ በኋላ ና።" አለው። ዑመር ቢን አልኸጧብ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ቦታው ላይ ነበሩና የዚህን አይነት ግብይይት አወገዙ። ለጦልሓም ብሩን አሁኑኑ እንዲሰጥ አልያም የወሰደውን ወርቅ እንዲመልስ ምሎ ነገረው። የዚህም ምክንያት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ብር በወርቅ መለዋወጥ ወይም በተገላቢጦሹ መለዋወጥ ተለዋዋጩ በቀጥታ መቀባበል እንዳለበት ያለበለዚያ ግን ይህ ግብይት የተከለከለው አራጣዊና ትክክል ያልሆነ ግብይት እንደሚሆን ማውሳታቸውን ስለዚህም ወርቅ በብር ብር በወርቅ እጅ በእጅ ካልሆነና የተሟላ የሆነ ቅብብል ከሌለ በቀር መገበያየት እንደማይፈቀድ፤ ልክ እንደዚሁ ስንዴ በስንዴ፣ ገብስ በገብስ፣ ተምር በተምር መለዋወጥ አምሳያውን በአምሳያው፣ ኪሎ በኪሎ፣ ስፍር በስፍር፣ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር መገበያየት እንደማይፈቀድ፤ ከነዚህ ውስጥ አንዳቸውም አንዱን አሁን አንዱን ዘግይቶ መሰጣጠት እንደማይፈቀድና ከመቀባበል በፊት መለያየትም አለመፈቀዱን ነቢዩ የአላህ ሶዋትና ሰላም (ሶለሏሁ ዓለይሂ ሰለም) ማውሳታቸውን ዑመር ገለፁ።