ዑሥማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ እጅግ በጣም የተብራራ እንዲሆን ተግባራዊ በሆነ መንገድ አስተማሩ። በውዱእ እቃ ውሀ እንዲያመጡላቸው ጠየቁ። ቀጥሎም በእጆቻቸው ላይ ሶስት ጊዜ አፈሰሱ። ከዚያም ቀኝ እጃቸውን እቃ ውስጥ ከተው ውሀ በማውጣት ውሀውን አፋቸው ውስጥ ከተው ካመላለሱ በኋላ ተፉት። ቀጥሎም ውሀውን ወደ አፍንጫቸው ውስጥ ከሳቡ በኋላ መልሰው አወጡት። ከዚያም ፊታቸውን ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እጃቸውን ከክርናቸው ጋር ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እጃቸውን አርጥበው ጭንቅላታቸው ላይ አንድ ጊዜ አበሱ። ከዚያም ሁለት እግሮቻቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው ጋር ሶስት ጊዜ አጠቡ። ዑሥማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ዉዱአቸውን ባጠናቀቁ ጊዜ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መልኩ ዉዱእ ሲያደርጉ እንደተመለከቱና በዚህ መልኩ ዉዱእ አድርጎ ልቡንም ጌታው ዘንድ ጥዶ በተመስጦ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው አላህ በዚህ የተሟላ ዉዱእና የጠራ ሶላት ምክንያት ያለፈውን ወንጀሉ በመማር እንደሚመነዳው እንዳበሰሯቸው ነገሯቸው።