explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአንድ አንድ ወቅቶች ዉዱእ ያደረጉ ጊዜ ሁሉንም የዉዱእ አካላቶቻቸው አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ያጥቡ ነበር። ፊታቸውን ‐ መጉመጥመጥና ውሀውን ወደ አፍንጫ ውስጥ ስቦ መልሶ ማውጣትን ጨምሮ‐ ፣ ሁለት እጃቸውንና ሁለት እግራቸውን አንድ አንድ ጊዜ ያጥቡ ነበር። ይህም ዝቅተኛው የግዴታ መጠን ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • አካላቶቻችንን ስናጥብ ግዴታ ያለብን አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ከዚህ በላይ መጨመር ተወዳጅ ነው።
  • በአንድ አንድ ወቅቶች ላይ አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ዉዱእ ማድረግ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
  • ጭንቅላትን በማበስ ዙሪያ የተደነገገው አንድ ጊዜ ብቻ ማበስ ነው።