ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሰዎች ሲናገሩ ሁለት ትላልቅ ደረጃዎችን ገለፁ። የመጀመሪያው: ዉዱእን በተደነገገው መልኩ አሳምሮ፣ አዳርሶ፣ አሟልቶ ያደረገ፤ ለሁሉም አካል የሚገባውን ውሃ የሰጠ ቀጥሎም «አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱላሂ ወረሱሉህ» ያለ ሰው በፈለገው በር እንዲገባ ለርሱ ስምንቱም የጀነት በሮች የሚከፈቱለት መሆናቸውን ነው። ሁለተኛ: ይህንን የተሟላ ውዱእ ያደረገና ቀጥሎ ከዚህ ዉዱእ በኋላ በቀልቡ ወደ አላህ ዞሮ፣ ለአላህ አጥርቶና ተመስጦ፣ በፊቱም በመላ አካሉም ተዋድቆ ሁለት ረከዓ ቆሞ ለአላህ የሚሰግድ ለርሱ ጀነት ግድ እንደምትሆንለት ይፋ አደረጉ።