ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገላቸውን ከአንድ ቁና ውሃ እስከ አምስት እፍኝ ድረስ ባለ ውሃ ያጥቡ ወይም ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዱእ ያደርጉ ነበር።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።