explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ወቅት ላይ ዉዱእ ያደረጉ ጊዜ ሁሉንም የዉዱእ አካላቶቻቸው ሁለት ሁለት ጊዜ ያጥቡ ነበር። ፊታቸውን ‐ መጉመጥመጥና ውሀውን ወደ አፍንጫ ውስጥ ስቦ መልሶ ማውጣትን ጨምሮ‐ ፣ ሁለት እጃቸውንና ሁለት እግራቸውን ሁለት ሁለት ጊዜ ያጥቡ ነበር።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • አካላቶቻችንን ስናጥብ ግዴታ ያለብን አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ከዚህ በላይ መጨመር ተወዳጅ ነው።
  • አንድ አንድ ወቅት ላይ ሁለት ሁለት ጊዜ ዉዱእ ማድረግ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
  • ጭንቅላትን በማበስ ዙሪያ የተደነገገው አንድ ጊዜ ብቻ ማበስ ነው።