ሙስሊሞች በነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘመንና ከርሳቸው በኋላም በቅን ኸሊፋዎቹ ዘመን ዘካተል ፊጥርን ለትንሹም ሆነ ለትልቁ አንድ ቁና ስንዴ ያወጡ ነበር። በዛን ወቅት ምግባቸው ገብስ፣ (ዘቢብ) የደረቀ ወይን፣ ("አቂጥ") የደረቀ ወተት (እርጎ)ና ተምር ነበር። የአንድ ቁና መጠን በእፍኝ ሲሰላ አራት እፍኝ ነው። እፍኝ ማለት ደግሞ መካከለኛ እጅ ያለው ወንድ በሁለት እጁ ሙሉ ማለት ነው። ሙዓዊያ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ኸሊፋ በነበሩበት ወቅት ወደ መዲና ሲመጡ በጊዜውም የሻም ስንዴ የበረከተበት ወቅት ነበረና ኹጥባ አደረጉ፡ "የሻም ስንዴ ሁለት እፍኝ (ግማሽ ቁና) ከአንድ ቁና ተምር ጋር ይስተካከላል ብዬ አምናለሁ።" አሉ። ሰዎችም በርሳቸው አቋም ላይ ተገበሩ። አቡ ሰዒድ አልኹድሪይም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፡ "እኔ ግን እስከኖርኩ ድረስ በነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘመን አወጣው የነበርኩትን ያህል ማውጣቴን አላቆምም።"