ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከረመዷን በኋላ ዘካተል ፊጥርን ግዴታ አደረጉ። መጠኑም አራት እፍኝ የሚያህል አንድ ቁና ነው። አንድ እፍኝ፡ ማለት የመካከለኛ ሰው መዳፍ የሚሞላ ነው። ግዴታ ያደረጉትም ሁሉም ነፃ፣ ባሪያ፣ ወንድ፣ ሴት፣ ህፃን፣ ትልቅ ሙስሊም ላይ ከተምር ወይም ከገብስ እንዲሰጡ ነው። ይህም እርሱ ዘንድ ያለው ከቀንና ከምሽት ቀለቡ የሚተርፍ በሆነ ላይ ለነፍሱና ለሚያስተዳድራቸው ሁሉ ነው። ሰዎች ወደ ዒድ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።