ዐምር ቢን ሹዐይብ ከአባቱ፣ አባቱም ከአያቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!" ሐሰን ነው። - አቡዳውድ ዘግበውታል።