ከቡረይደህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'" ሶሒሕ ነው። - ቲርሚዚ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሙስሊሞችና በሌሎች ከሀዲያንና መናፍቃን መካከል ያለው መተማመኛና ቃል ኪዳን ሶላት እንደሆነና ሶላትን የተወ ሰውም በርግጥ እንደካደ ገለፁ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የሶላት ጉዳይ ትልቅ እንደሆነና በአማኝና በከሀዲ መካከል መለያም እንደሆነ እንረዳለን።
  • የሙስሊምነት ፍርድ በሰውዬው ውስጣዊ ማንነት ላይ ሳይሆን ውጫዊ ማንነቱ ላይ በመንተራስ እንደሚፀና እንረዳለን።