ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በኡመታቸው ውስጥ አንዳንድ ተግባራት የፈፀሙ ሰዎችን "ከኛ አይደሉም!" በማለት ዛቱ። ከተግባራቱም፦ የመጀመሪያው: "ገድ ተግባር የፈፀመ ወይም ለሱ የተፈፀመለት" የዚህ አመለካከት መሰረት:- ጉዞ ወይም ንግድ ወይም ከዚህ ውጪ ያለን ስራ ለመጀመር በራሪን ይለቃል፤ በራሪው ወደ ቀኝ አቅጣጫ ከበረረ ተስፋን በመሰነቅ ወደ ሚፈልገው አላማ ይሄዳል። ወደ ግራ አቅጣጫ ከበረረ ገደ ቢስነትን በማመን የሚፈልገውን አላማ ከመፈፀም ይቆጠባል። ይህን ተግባር ራሱም ይሁን ለርሱ የሚሰራለትን በመመደብም መፈፀም አይፈቀድም። በማንኛውም በራሪዎች ወይም እንስሳዎች ወይም በአካል ጉዳተኞች ወይም በቁጥሮች ወይም በቀናት ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ በሚሰማም ይሁን በሚታይ በሆነ ነገር ገደ ቢስነትን ማመን እዚህ ውስጥ ይካተታል። ሁለተኛው: "የጠነቆለ ወይም ያስጠነቆለ።" ከዋክብትንና ሌሎች ነገሮችን በመጠቀም የሩቅ እውቀትን የሞገተ ሰው ወይም እንደ ጠንቋይና የመሳሰሉት የሩቅን እውቀት ወደ ሚሞግቱ ሰዎች የሄደና የሩቅን እውቀት ሞግቶ በሚናገረው ያመነ በሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ በወረደው በርግጥ ክዷል። ሶስተኛ: "የደገመ ወይም የተደገመለት" እሱም አንድን ሰው ሊጠቅም ወይም ሊጎዳ የድግምትን ተግባር በራሱ የፈፀመ ወይም ለሱ ድግምት የሚሰራለትን የመደበ ሰው ወይም ትብታብን ተብትቦ የቋጠረና ክልክል የሆኑ መነባንቦችን በማነብነብና እርሱ ላይ በመትፋት የደገመበት ሰው ነው።