ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጀምረተል ዐቀባህ መወርወሪያ ንጋት ላይ ግመላቸው ላይ ሆነው 'ጠጠር ልቀምልኝ!' አሉኝ። ሰባት ጠጠርም ለቀምኩላቸው። እነርሱም ትናንሽ በጣት መሀል የሚወረወሩ ጠጠሮች ነበሩ። መዳፋቸው ላይ አኑረው እያገላበጧቸውም 'መጠናቸው በነዚህ ልክ ያሉ ጠጠሮችን ወርውሩ!' አሉ። ቀጥለውም 'እናንተ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነው።' አሉ።" ሶሒሕ ነው። - ኢብኑ ማጀህ፣ ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የመሰናበቻ ሐጅ ወቅት የእርድ ቀን ጀምረተል ዐቀባ ንጋት ላይ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር እንደነበረ ተናገሩ። የሚወረውሩት ጠጠር እንዲለቅምላቸው አዘዙት። እርሱም ሰባት ጠጠሮች ለቀመላቸው። እያንዳንዱም ጠጠር የሽንብራ ወይም የለውዝ ፍሬ መጠን ነበር ያላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በእጃቸው ላይ አኑረውት ጠጠሮቹን መዳፋቸው ላይ እያንከባለሉ እንዲህ አሉ: የምትወረውሩት ጠጠር በዚህ ልክ ይሁን። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ወሰን ከማለፍና ከማክረር አስጠነቀቁ። የቀደሙ ህዝቦችን ያጠፋው ወሰን ማለፍና በሃይማኖት ላይ ከልክ በላይ ማክረር መሆኑንም ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ መከልከሉንና ፍፃሜው የከፋ መሆኑን እንዲሁም ለጥፋትም ምክንያት መሆኑ መገለፁ።
  • ከወደቁበት ስህተት ለመራቅ ሲባል ከቀደሙን ህዝቦች ትምህርት መውሰድ ተገቢ መሆኑን እንረዳለን።
  • ሱናን በመከተል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።