ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአንዳንድ የድንቁርና ዘመን ሰዎች ተግባር አስጠነቀቁም ከለከሉም። እንዲህም አሉ: እነዚህ ከኛ አይደሉም: የመጀመሪያው: ጉንጩን የመታ ነው። ጉንጭን የለዩት በአብዛኛው የሚፈፀመው እርሱ ስለሆነ ነው እንጂ የተቀሩትን የፊት ክፍልን መምታትም ክልከላው ውስጥ ይካተታል። ሁለተኛው: ልብስ ላይ ጭንቅላት እንዲገባበት ተብሎ የሚከፈተውን (አንገትያ) ከትእግስት ማጣት ብዛት መቅደድ ነው። ሶስተኛው: የድንቁርና ዘመን ጥሪዎችን መጣራት ነው። ለምሳሌ ያህል፦ ወዮልኝ፣ ወይኔ በጠፋው ማለት፣ ሙሾ ማውረድ፣ እየገጠሙ ማለቃቀስና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።