ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላትን ከመተው አስጠነቀቁ። በሰውዬውና ሺርክና ክህደት ላይ በመውደቅ መካከል ያለው ግርዶ ሶላትን መተው እንደሆነም ተናገሩ። ሶላት ከኢስላም ማእዘናቶች መካከል ሁለተኛው ማእዘን ነው፣ ሶላት በኢስላም ትልቅ ጉዳይ ነው። ግዴታነቱን አስተባብሎ የተወ ሰው በሁሉም ዑለማእ (የኢስላም ሊቃውንት) ስምምነት መሰረት ክዷል። በስንፍናና ድክመት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ የተወም እንደዚሁ ከሀዲ ነው። በዚህ ዙሪያ የሶሐቦች ሙሉ ስምምነት እንዳለም ተሰምቷል። አንዳንዴ የሚተው አንዳንዴ የሚሰግድ ከሆነ ደግሞ ለዚህ ከባድ ዛቻ የተጋረጠ ይሆናል።