ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በሰዎች ውስጥ ሁለት ነገሮች አሉ፤ እነርሱም ክህደት ናቸው። በዘር መተቸትና በሞተ ላይ ሙሾ ማውረድ ናቸው።"» ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሰዎች መካከል ስለሚገኙ ሁለት የከሃዲያን ስራዎችና የድንቁርና ዘመን ስነ ምግባሮች ተናገሩ። እነርሱም: የመጀመሪያው: ሰዎችን በዘራቸው መተቸት፣ ማሳነስና በዘር እነርሱ ላይ መኩራራት ነው። ሁለተኛው: በመከራ ወቅት የአላህን ውሳኔ በማማረር ድምፅን ከፍ ማድረግ ወይም ከትእግስት ማጣት ብዛት ልብስን መቅደድ ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ለሰዎች በመተናነስና በሰዎች ላይ ባለመኩራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • በመከራ ላይ መታገስና አለመበሳጨት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  • እነዚህ ተግባራት ከትንሹ ክህደት ነው የሚመደቡት። ከትንሹ ክህደት ክፍሎች መካከል አንድ ስራን የሰራ ሰው ደሞ ትልቁን ክህደት እስኪሰራ ድረስ ከእስልምና የሚያስወጣ ክህደትን የካደ አይሆንም።
  • እስልምና በዘር መተቻቸትና የመሳሰሉትን በሙስሊሞች መካከል መከፋፈልን የሚፈጥሩ ነገሮችን ሁሉ ከልክሏል።