ከአቡዘር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምተዋል: "አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።