explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለማስፈራራት ወይም ንብረታቸውን ለመቀማት በሙስሊሞች ላይ መሳሪያ ከማንሳት አስጠነቀቁ። ያለ አግባብ ይህንን የፈፀመም ትልቅ ሀጢአትንና ወንጀልን መፈፀሙን ለዚህ ከባድ ዛቻም መጋረጡን አሳሰቡ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ሙስሊም ከሙስሊም ወንድሙ ጋር መጋደሉ ብርቱ ማስጠንቀቂያ የመጣበት ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
  • በምድር ላይ ከሚሰሩ ትላልቅ ወንጀሎችና ብክለቶች መካከል መሳሪያን በሙስሊሞች ላይ ማንሳትና በመግደል ማበላሸት አንዱ ነው።
  • የተጠቀሰው ዛቻ ወሰን አላፊዎችን፣ አጥፊዎችንና ሌሎችም የመሳሰሉትን በሀቅ (በሸሪዓ በተፈቀደ ምክንያት) መጋደልን አያካትትም።
  • ለቀልድ እንኳ ቢሆን ሙስሊሞችን በመሳሪያ ወይም በሌላ ነገር ማስፈራራት መከልከሉን እንረዳለን።