ከዑክልና ዑረይና ጎሳ የሆኑ ሰዎች ሰልመው ወደ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መጡ። ሆዳቸውን የነፋፋች በሽታ አመማቸው። የመዲናም ምግብና አየር ስላልተስማማቸው መዲና መቆየትን ጠሉ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለዘካ ወደ ተሰበሰበ ግመል ሄደው የግመል ሽንትና ወተት እንዲጠጡ አዘዟቸው። እነርሱም ወደዛ ሄዱ። ጤነኞች የሆኑ፣ የወፈሩና መልካቸውም የተመለሰ ጊዜ የነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እረኛ ገለው ግመሉን እየነዱ ሄዱ። ወሬውም የቀኑ መጀመሪያ ላይ ተሰማ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እነርሱን ለመፈለግ ሰዎች ላኩ። የተላኩትም ሰዎች አገኟቸው። ረፋድ የሆነ ጊዜ ተማርከው ወደ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መጡ። እረኛው ላይ በፈፀሙት መልኩ እጆቻቸውና እግሮቻቸው እንዲቆረጥ፤ አይኖቻቸው እንዲጠፋ አዘዙ። ሀሩራማ ድንጋይ ላይም ተጣሉ። እስኪሞቱ ድረስም ውሃ እንዲያጠጧቸው ሰውን ቢማፀኑም ማንም አላጠጣቸውም። አቡ ቂላባም እንዲህ አለ: "እነዚህ ሰዎች ሰረቁ፤ ገደሉ፤ ከእምነት በኋላም ካዱ፤ አላህና መልክተኛውንም ተዋጉ።"