explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዐስርን ሶላት ሆን ብሎ ወቅቱን ከማዘግየት አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመ ሰው ስራው ተበላሽቶ ከንቱ ይቀራል።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የዐስርን ሶላት በመጀመሪያ ወቅቱ በመጠባበቅ ላይና ወደዚህ ተግባር በመቻኮል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • የዐስርን ሶላት በተወ ሰው ላይ ብርቱ ዛቻ መምጣቱንና ዐስርን ከወቅቱ ማሳለፍ ሌሎችን ሶላቶች ከወቅቱ ከማሳለፍ የበለጠ እጅግ ከባድ መሆኑን እንረዳለን። የዐስር ሶላት {በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡} [አልበቀራህ: 238] በሚለው የአላህ ንግግር ላይ ባለው ትእዛዝ ልዩ ሆና የተወሳች ምርጧ ሶላት ናትና።