የትኛውንም የግዴታ ሶላት ወቅቱ እስኪወጣ ድረስ መስገድን የረሳ ሰው ባስታወሰ ወቅት ቀዷእ ለማድረግ መፍጠን እንደሚገባውና አንድ ሙስሊም በወቅቱ መስገድን በመተዉ ለፈፀመው ወንጀልም ባስታወሰ ወቅት መስገዱ እንጂ ሌላ ምንም ማበሻና ማስማሪያ እንደሌለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ። አላህ በተከበረው መጽሐፉ እንዲህ ብሏል {ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማስታወስ ስገድ።} [ጣሀ:14] ማለትም የተረሳን ሶላት ባስታወስካት ወቅት ቀጥ አድርገህ ስገድ ማለትም ነው።