ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋ ድረስ ምሽቱን የተኛ ሰውዬ ተወሳ። እርሳቸውም "ይህ ሸይጧን ጆሮዎቹ ውስጥ ወይም ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው።" አሉ።» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።