ከአቡ ሙሳ አል-አሽዓሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።