ኡበይ ቢን ከዕብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተናገሩት: "አንድ ቤቱ ከመስጂደ ነበዊይ እጅግ የራቀ ከአንሷር የሆነ ሰውዬ ነበር። አንድም ሶላት አታመልጠውም ነበር። ይልቁኑም ሁሉንም ሶላት ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተገኝቶ ይሰግድ ነበር። ለርሱም እንዲህ ተባለ: እንደው በምሽቱ ጨለማና ቀን ላይ መሬቱ በሚግልበት ወቅት የምትጋልበው አህያ ብትገዛ አይሻልም? እርሱም እንዲህ አለ: "ቤቴ ከመስጂዱ ጎን ቢሆን አያስደስተኝም። እኔ ወደ መስጂድ ስመጣ የምራመደው እርምጃና ወደ ቤተሰቦቼ ስመለስም የምራመደው እርምጃ እንዲፃፍልኝ እፈልጋለሁ።" አለ። ንግግሩም ነቢዩ ዘንድ ደረሰ። እርሳቸውም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "በርግጥም አላህ ይህንን ሁሉ ላንተ ሰብስቦልሃል።"