(መኖሪያው) ገጠራማ ስፍራ የሆነ አንድ ሰው ጀነት የሚያስገባውን ስራ እንዲጠቁሙት ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መጣ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጀነት መግባትና ከእሳት መዳን የኢስላም ማእዘናትን በመፈፀም ላይ የተገደበ እንደሆነ መለሱለት። አላህን በብቸኝነት መገዛትና በርሱ ላይ አንዳችንም አለማጋራት፣ በሁሉም ቀንና ምሽቶች አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረገውን አምስቱን ሶላቶች መስገድ፣ አላህ በአንተ ላይ ግዴታ ያደረገውን የገንዘብ ዘካ ለሚገባው ሰው መስጠት፣ የረመዷን ወርን በወቅቱ በመጾም ላይ መጠባበቅ ናቸው። ሰውዬውም "ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! ከእርሶ ከሰማሁት ግዴታ አምልኮዎች አንዳችም ስራ አልጨምርምም አልቀንስምም።" አለ። ዞሮ የሄደ ጊዜም ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ከጀነት ባለቤቶች መካከል የሆነን ሰው መመልከት ያስደሰተው ወደዚህ ባላገር (የገጠር) ሰውዬ ይመልከት።"