ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና መዚይ (ነጭ፣ ቀጭን፣ የሚዝለገለግ፣ ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት ወይም ከግንኙነት በፊት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) ብዙ ጊዜ ይወጣቸው እንደነበር ተናገሩ። መውጣቱን ተከትሎ እንዴት ማድረግ እንዳለባቸውም አያውቁም። የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ልጅ ፋጢማ ባለቤት ስለሆኑ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጠየቅ አፈሩ። ሚቅዳድ ቢን አስወድ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለዚህ ጉዳይ እንዲጠይቅላቸው አድርገው ላኩት። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ብልቱን አጥቦ ዉዱእ ማድረግ እንደሚገባው በመንገር መልስ ሰጡት።