ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአንድ የመዲና መንገድ ላይ አቡ ሁረይራን - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አገኙ። አቡ ሁረይራም ጀናባ (የዘር ፈሳሽ ወጥቶት ገላውና ያልታጠበ) ላይ ስለነበር ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከነበረው ክብርና ልቅና የተነሳ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ከርሳቸው ጋር መቀማመጡንና ማውራቱን ጠላ። ተደብቆ በመሄድም ታጠበና ከዚያም ተመልሶ መጣና ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የት ሄዶ እንደነበር ጠየቁት። የነበረበትንም ሁኔታ ነገራቸው። እርሱ በጀናባ ምክንያት ተነጅሶ ስለነበር ከርሳቸው ጋር መቀማመጥ ጠልቶ መሆኑን ነገራቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመደነቅ እንዲህ አሉት: አማኝ ሰው በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን በሕይወትም ሆነ ሞቶ ንፁህ ነው አይነጀስም።