ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው: "ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።"» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጁሙዓን ሶላት ለመስገድ የሚመጣ ሰው ለጀናባ እንደሚታጠበው ትጥበት አምሳያ መታጠብ ለርሱ ተወዳጅ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተው ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የጁሙዓ ትጥበት አፅንዖት የተሰጠው ጉዳይ እንደሆነ፤ የጁሙዓ ቀን መታጠብ ለአማኞች ሱና እንደሆነና ወደ ሶላት በሚሄድበት ጊዜ መሆኑ በላጭ እንደሆነ እንረዳለን።
  • በንፅህና እና በመልካም መዓዛ ላይ መጣር ከሙስሊም ስነምግባርና ስነስርዓት መካከል ነው። ሰዎችን በሚገናኙበት ወቅትና በሚቀማመጡበት ወቅት በተለይም በጁሙዓና በጀማዓ ሶላቶች ወቅት ደግሞ ትእዛዙ አፅንዖት ይኖረዋል።
  • ሐዲሡ የሚመለከተው ጁሙዓ ግዴታ ለሆነባቸው ሰዎች ነው። ይህም በጁሙዓ መገኘት የሚጠበቅበት እርሱ ስለሆነ ነው።
  • ጁሙዓ ለሚመጣ ሰው ንፁህ መሆኑ፣ መጥፎ ጠረኖች ከሰውነቱ እስኪወገድ ድረስ መታጠብ፣ ሽቶ መቀባቱ ይወደድለታል። ዉዱእ ብቻ ካደረገም ይበቃለታል።