ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ መታጠብን በፈለጉ ጊዜ እጃቸውን በመታጠብ ይጀምሩ ነበር። ቀጥለውም ልክ ለሶላት እንደሚያደርጉት አምሳያ ዉዱእ ያደርጉ ነበር። ቀጥለውም ውሃን በሰውነታቸው ላይ ያፈሳሉ። ቀጥለው የጭንቅላታቸውን ፀጉር በእጆቻቸው ይፈለፍላሉ። ውሃው ወደ ፀጉራቸው ስር መድረሱንና የጭንቅላታቸውን ቆዳ ማራሱን ያሰቡ ጊዜ በጭንቅላታቸው ላይ ሶስት ጊዜ ውሃን ያፈሳሉ። ቀጥለው ቀሪ ሰውነታቸውን ያጥባሉ። ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - "እኔና የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአንድ እቃ ሁለታችንም እየዘገንን እንታጠብ ነበር።" ብላለች።