የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ለአቅመ አዳም የደረሰና አዕምሮው ጤነኛ በሆነ ሙስሊም ላይ ሁሉ በሳምንት ውስጥ ካሉት ሰባት ቀናት አንዱን ቀን የመታጠብ የጠበቀ ሀቅ እንዳለበት ተናገሩ። በዚህ ቀንም ንፅህናንና ፅዳትን በመፈለግ ጭንቅላቱንና ሰውነቱን ይታጠባል። ይህንን ሀሳብ ከሚያንፀባርቁ አንዳንድ ዘገባዎች እንደምንረዳው ከነዚህ ቀናቶች ሁሉ ለመታጠብ በላጩ ቀን የጁሙዐ ቀን ነው። ለምሳሌ ያህል ሀሙስ ቀን እንኳ ታጥቦ የጁሙዐ ቀን ከሶላት በፊት መታጠቡ አፅንኦት የተሰጠው ተወዳጅ ጉዳይ ነው። የጁሙዐ ቀን መታጠብን ከግዴታነት የሚያዞረው (ግዴታ አለመሆኑን የሚያሳየው) የእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና እንዲህ የሚለው ንግግር ነው "ሰዎች ነፍሶቻቸውን ለመቀለብ የሚሰሩ ነበሩ። ወደ ጁሙዐ የመጡ ጊዜም በዛው በስራ ድባባቸው ይመጡ ነበር። ለነርሱም 'ብትታጠቡስ' ተባሉ።" (ቡኻሪ ዘግበውታል) በሌላ ዘገባቸው "እየሸተቱም ይመጡ ነበር።" ማለትም የላብና የመሳሰሉት ሽታ እየሸተቱ ይመጡ ነበር። ከዚህ ሁኔታቸው ጋርም ሆነው "ብትታጠቡስ" መባላቸው ከነርሱ ውጪ ያለው ግዴታው ላይሆን ይበልጥ የተገባ ነው።