ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።"» ሙስሊም ባስተላለፉት ደግሞ "አንዱን በአፈር በመቀላቀል ይጠበው።" የሚል ተዘግቧል። ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።