ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዙልሒጃ ወር የመጀመሪያ አስር ቀናቶች ውስጥ መልካም ስራዎችን መስራት በአመቱ ውስጥ ከሚገኙ ቀናቶች ሁሉ የበለጠ መሆኑን ገለፁ። ሰሐቦችም አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከነዚህ አስር ቀናት ውጪ ጂሃድ ማድረግ ወይስ ከጂሃድ ውጪ ያሉ መልካም ስራዎችን በነዚህ ቀናት ውስጥ መስራት የትኛው ይበልጣል? ብለው ጠየቁ። ይህም እነርሱ ዘንድ ጂሃድ ከሁሉም በላጭ ስራ መሆኑ የተረጋገጠ ጉዳይ ስለሆነ ነው። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም በነዚህ ቀናቶች መልካም ስራዎችን መስራት ከነዚህ ውጭ ባሉት ቀናት ከሚደረግ ጂሃድም ይሁን ሌሎች ስራዎች የበለጠ እንደሆነ ተናገሩ። ይህ ግን በአላህ መንገድ ገንዘቡንና ነፍሱን አጋልጦ ሙጃሂድ ሆኖ የወጣና በአላህ መንገድ ገንዘቡንም ያጣ ነፍሱንም የሰዋ ሲቀር ነው። በነዚህ ከፍ ባሉት ቀናቶች የሚሰሩ ስራዎችን የሚበልጠው ይህ ነው።