ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ ለሚዘምት ሰው መሳሪያ፣ መጓጓዣ፣ ምግብ፣ ቀለብና ሌሎችም ለጉዞው የግድ የሚያስፈልገውን ነገር ያሰናዳ ሰው ልክ እንደዘማቹ እንደሚቆጠርና የዘማቾቹን ምንዳ እርሱም እንደሚያገኝ ተናገሩ። የዘማችን ጉዳይ በመልካም ሊሸፍን ሃላፊነት የወሰደ ሰውና እርሱ (ዘማቹ) በራቀበት ወቅት ቤተሰቦቹን ሊንከባከብ የርሱን ቦታ የተተካ ሰውም ልክ እንደዘማች እንደሚቆጠር ተናገሩ።