explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ግንኙነትና ፆታዊ ስሜትን የሚያነሳሱን ያልፈፀመ - "ረፈሥ" የሚለው ቃል ፆታዊ ግንኙነትንም ይሁን መሳሳምና መተሻሸትን የመሰሉ የግንኙነት መንደርደሪያዎችን እንዲሁም ፀያፍ የቃል አጠቃቀምንም የሚያጠቃልል ቃል ነው። ወንጀልና ኃጢዓት በመፈፀም - ሳያምፅ ‐ ሐጅን ያከናወነ ያለውን ደረጃ ገለፁ። አመጽ ውስጥ ከሚካተቱት መካከል በኢሕራም ጊዜ የተከለከለን ማድረግ ይገኝበታል። በዚህ መልኩ ሐጅን ያከናወነ ሰው ልክ ህፃን ልጅ ከወንጀል የፀዳ ሆኖ እንደሚወለደው እርሱም ከወንጀሉ የተማረ ሆኖ ከሐጅ ይመለሳል።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ወንጀል ምንም እንኳ በማንኛውም ሁኔታ የተከለከለ ቢሆንም የሐጅን የአምልኮ ስርአት ለማላቅ ሲባል በሐጅ ወቅት ክልክልነቱ የበረታ እንደሚሆን እንረዳለን።
  • የሰው ልጅ ሲወለድ ከወንጀል የፀዳ ሆኖ የሚወለድ በመሆኑ የሌላ ሰው ወንጀል የሚጫንበት እንዳልሆነ እንረዳለን።