ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የሐጅና የዑምራን አምልኮ አቀራርቦ በመፈፀምና ከቻሉ ሳያቆራርጡ በመፈፀም ላይ አነሳሱ። ምክንያቱንም ሲገልፁ ብረትን በወናፍ እሳት መንፋት ብረቱ ላይ የተቀላቀለውን ባዕድ የማዕድን ቆሻሻ ለማስወገድ ምክንያት እንደሆነው ሁሉ እነርሱንም መፈፀም ድህነትንና ወንጀልን እንዲሁም ወንጀል በቀልብ ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ለማስወገድ ምክንያት መሆናቸውንም ገለፁ።