ከምእመናን እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጂሀድን እጅግ በላጭ ስራ አድርገን ነው የምናስበውና እኛም (ሴቶች) ከሀዲያንን እንታገልን?" እርሳቸውም፦ "በፍፁም! ነገር ግን እጅግ በላጩን ጂሀድ (ታገሉ!) (እርሱም) ተቀባይነት ያለው ሐጅ ነው።" አሉ። ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ሰሐቦች (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና) በአላህ መንገድ መታገልንና ጠላቶችን መጋደልን እጅግ በላጭ ከሆኑ ተግባራቶች መካከል እንደሆነ አድርገው ይመለከቱ ነበር። ዓኢሻም (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴቶችም ጂሃድ ማድረግ ሊፈቀድላቸው ዘንድ ጠየቀች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሴቶች እጅግ በላጭ የሆነውን ጂሀድ ጠቆሟቸው: እርሱም ቁርኣንና ሐዲሥን የገጠመውና ከወንጀልና ከይዩልኝ የፀዳው ተቀባይነት ያለውን ሐጅ ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ለወንዶች ጂሃድ እጅግ በላጭ ከሚባሉ ስራዎች መሆኑን እንረዳለን።
  • ለሴቶች ደግሞ ሐጅ ማድረግ ከጂሀድም ይበልጣል። ለሴቶች እጅግ በላጩ ተግባር ሐጅ ማድረግ ነው።
  • ሥራዎች እንደ ሠሪው ሁኔታ ይበላለጣሉ።
  • ሐጅ ጂሃድ (ትግል) ተብሎ የተጠራው ነፍስን መታገል ስለሆነ ነው። ሐጅ ለማድረግ ገንዘብና የሰውነት አቅም ያስፈልጋል። ሐጅ ልክ በአላህ መንገድ እንደመዋጋት አካላዊና ገንዘባዊ አምልኮ ነው።