ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመሰናበቻ ሐጅ የተመለሱ ጊዜ ሐጅ ላላደረገች ከአንሷር ለሆነች ሴት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" አሏት። ሁለት ግመል እንደነበራቸው፤ ባሏና ወንድ ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ እንዳደረጉና ሌላኛውን ደግሞ ከጉድጓድ ውሃ እንዲያመላልሱበት እንደተወላቸው በመንገር ያልሄደችበትን ምክንያቷን ገለፀችላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዑምራን በረመዳን ወር በመፈፀም የሚገኘው ምንዳ የሐጅን ምንዳ የሚስተካከል እንደሆነ ነገሯት።