ዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።" ሐሰን ነው። - አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ አሕመድ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ቁርኣንን ለሚያነብ፣ ቁርኣን ውስጥ ባለው ለሚሰራ፣ በቃሉ መሸምደድንም ሆነ አሳምሮ ማንበብን አጥብቆ የያዘ ጀነት በሚገባ ጊዜ "ቁርኣንን አንብብ! በዚህም ሰበብ የጀነት ደረጃዎችን ውጣ! ቁርኣንን በስክነትና እርጋታ ዱንያ ላይ ታነበው እንደነበርከው አንብብ! ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል በማለት ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በቁጥርም ሆነ በሁኔታ ለሥራችን በሚመጥን መልኩ ነው የምንመነዳው።
  • ቁርኣንን በማንበብ፣ አሳምሮ በመቅራት፣ በመሸምደዱ፣ በማስተንተኑና በቁርኣን በመስራት ላይ መበረታታቱን እንረዳለን።
  • ጀነት በርካታ ደረጃዎችና እርከኖች ያሏት ሲሆን የቁርኣን ባለቤት የሆነ ሰው ከፍተኛ የሆነውን ደረጃ ነው የሚያገኘው።