አንድ ሰውዬ ሲሰራው አላህም የሚወደው ሰዎችም የሚወዱት የሆነን ስራ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲጠቁሙት ጠየቀ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደዱንያ ትርፍ የሆኑ እንደ አኺራም የማይጠቅሙ የሆኑ ነገሮችን በተውክና ዲንህ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉብህን ነገሮች የተውክ ጊዜ አላህ ይወድሃል። ሰዎች እጅ ያለን የዱንያ ጥቅም ችላ ያልክ ጊዜ ደሞ ሰዎች ይወዱሃል። ምክንያቱም ሰዎች በተፈጥሯቸው ንብረታቸውን ይወዷታልና በንብረታቸው የተጋፋቸውን ይጠሉታል። ንብረታቸውን የተወላቸውን ደግሞ ይወዱታል በማለት መለሱለት።