ከዐብደላህ ቢን ሚሕሰን አልአንሷሪይ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "ከናንተ መካከል ሰውነቱን ጤነኛ ሆኖ፤ በነፍሱና በቤተሰቡ ላይ ደህና ሆኖ፤ የእለት ቀለቡ እርሱ ዘንድ ኑሮ ያነጋ ሰው ዱንያን በሙሉ እንደተረከባት ይቁጠር።" ሐሰን ነው። - ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።