ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱዓእ አምልኮ እንደሆነ ተናገሩ። በዱንያና በአኺራዊ ጉዳዮች የሚጠቅመውን ነገር እንዲሰጠውና የሚጎዳውን ነገር እንዲከላከልለት አላህ የሚጠየቅበት ልመናዊ ዱዓም ይሁን፤ ማንኛውም ውጫዊና ውስጣዊ ንግግርም ተግባርም አላህ የሚወዳቸውና የሚያስደስተው ልባዊ፣ አካላዊና ገንዘባዊ አምልኮዎችን የሚያደርጉበት አምልኳዊ ዱዓእም ቢሆን ያው ነው። እነዚህ የዱዓእ አይነቶችም ለአላህ ብቻ ጥርት ተደርገው መፈፀማቸው ግዴታ ነው። ከዚያም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለዚህ ንግግራቸው የአላህን ንግግር ማስረጃ አደረጉ። አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ጌታችሁም አለ "ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።"}