ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሞተ ሰው በመሞቱ ስራው እንደሚቋረጥ፤ ከነዚህ ሶስት ስራዎች ውጪም ከሞተ በኋላ ምንዳ የሚያገኝበት እንደሌለው ተናገሩ። ሶስቱ ስራዎች ግን ሰበባቸው እርሱ ስለሆነ አይቋረጡም። የመጀመሪያው: እንደወቅፍ፣ መስጂድ መገንባት፣ ጉድጓድ መቆፈርና ሌሎች ምንዳቸው የማይቋረጥና የሚዘወትር ምፅዋት ናቸው። ሁለተኛው: ጠቃሚ ዕውቀትን ያስተላለፈ፡ ዕውቀት ሰጪ መጽሐፍትን እንደመፃፍ፣ የሆነን ግለሰብ ማስቀራትና ከሞተ በኋላ ይህ የቀራው ግለሰብ እውቀቱን በማሰራጨት ላይ መሳተፍን የመሰለ ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት ነው። ሶስተኛው: ለወላጆቹ ዱዓ የሚያደርግ አማኝ መልካም ልጅ ነው።