explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአምልኮዎች መካከል ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ እጅግ በላጭ የሆነ አምልኮ አንድም እንደሌለ ገለፁ። ምክንያቱም ዱዓእ የአላህን መብቃቃት፣ የባሪያን ደካማነትና ፈላጊነት እውቅና መስጠትን ውስጡ ስለያዘ ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የዱዓእን ትሩፋት እንረዳለን። አላህን የለመነ ሰው አላህን እያላቀ ነው። የሌለው አይከጀልምና ጥራት የተገባው አምላክ እጅግ የተብቃቃ መሆኑን እየመሰከረ ነው። ደንቆሮ አይለመንምና እጅግ ሰሚ መሆኑን፣ ስስታም አይለመንምና ቸር መሆኑን፣ ልበደረቅ አይለመንምና አዛኝ መሆኑን፣ ደካማ አይለመንምና ቻይ መሆኑን፣ ሩቅ ያለ አይሰማምና ቅርብ መሆኑን እና ሌሎችም የልቅናና የምሉዕነት መገለጫዎችን ለአሏህ እያረጋገጠ ነው።