ኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እናቱ ዐምረህ ቢንት ረዋሓ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - አባቱ ከገንዘቡ የተወሰነ ስጦታን ለልጇ እንዲሰጥ እንደጠየቀችው ተናገረ። ስለከበደው አንድ አመት ካዘገየ በኃላ ፍላጎቷን በማሟላት ለልጁ ኑዕማን ስጦታ መስጠት ታየው። እርሷም እንዲህ አለች: "ለልጄ በምትሰጠው ስጦታ የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እስክታስመሰክር ድረስ አልወድም።" እኔም በዛን ግዜ ህፃን ነበርኩኝ። አባቴ እጄን ይዞ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዚህ ልጅ እናት ቢንት ረዋሓ ለልጇ በምሰጠው ስጦታ እርሶን ማስመስከሬን ወደደች።" እርሳቸውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "በሺር ሆይ! ከዚህ ልጅ ውጪ ሌላ ልጅ አለህን?" እርሱም "አዎን" አለ። እርሳቸውም "ይህን የመሰለ ስጦታ ለሁሉም ልጆችህ ሰጥተሃልን?" አሉት። እርሱም "አይ" አለ። እርሳቸውም "እንዲህ ከሆነ አታስመስክረኝ። እኔ በግፍና በበደል ላይ አልመሰክርም።" አሉ። ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ ደግሞ እርሱን በመውቀስ መልኩ "ይልቁን በዚህ በደልህ ከኔ ውጪ ሌላን አስመስክር።" አሉት።