ጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ በተከፈተበት ዓመት መካ ሳሉ እንዲህ ሲሉ ሰማቸው "አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የበክት ሞራ መሸጥ ይፈቀድልናልን? ምክንያቱም በርሱ ጀልባዎቻችን ይጠገኑበታል፣ ቆዳዎቻችንን እንቀባለን፣ ሰዎች በርሱ ኩራዞቻቸውን ያበሩበታል።" ተባሉ። እርሳቸውም "በፍፁም እርሱን መሸጥም ክልክል ነው።" አሉና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጠል አድርገው እንዲህም አሉ: "አላህ አይሁዶችን ይርገማቸውና ያጥፋቸው አላህ በነርሱ ላይ የእንስሳ ሞራን የከለከለ ጊዜ አቅልጠው ቅባቱን ሸጡትና ዋጋውን በሉ።"