ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና: ከሁሉም የክራንቻ ጥርስ ባለቤት አውሬና ከሁሉም ባለጥፍር በራሪ ስጋ (መብላትን) ከልክለዋል።» ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የማንኛውንም በክራንቻ ጥርሶቹ አማካይነት የሚያድን አውሬና የማንኛውንም በጥፍሩ የሚቆርጥና የሚይዝ የሆነ በራሪ ስጋውን ከመብላት ከለከሉ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • እስልምና በምግቦች፣ በመጠጦችና በሌሎችም ነገሮች ላይ ሁሉ ጥሩውን በመጠቀም ማነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ክልክል መሆኑን ማስረጃ የጠቆመው ካልሆነ በቀር በምግብ ላይ መሰረቱ ፍቁድነት ነው።