ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሴት ልጅ ያለ ወሊዮቿ ፍቃድ ራሷን ማጋባቷን ከለከሉ። ጋብቻዋም ውድቅ ነው የሚሆነው። ጋብቻዋ እንዳልተፈፀመ ለመግለፅም ሶስት ጊዜ ደጋገሙት። ያለ ወሊዩዋ ፈቃድ አግብቷት የተገናኛትም በመገናኘቱ ምክንያት ለርሷ ሙሉ መህር ይሰጣታል። በመቀጠል የወሊዮች ደረጃ እኩል ሆኖ ጋብቻን በማሰሩ ዙሪያ ወሊዮች ከተጨቃጨቁ ጋብቻውን የሚያስረው የቀደመው ነው። ይህም ጥሩ ነገር አይቶላት ከሆነ ነው። ወሊዩዋ ከማጋባት ከታቀበ ወሊይ እንደሌላት ትቆጠራለች። መሪው ወይም ዳኛው ወይም የመሳሰሉት ወሊዩዋ ይሆናሉ። ያለበለዚያ ወሊይ እያለ መሪ ወሊይነት የለውም።